ዌንዳንና ያዋን ከኦሴል መጥተው ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር፤ ቀልጦ የተሠራ ብረትን፣ ብርጕድንና ከሙንን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤ በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።
ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የአደስና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ።
“ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋራ የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።
“ ‘ያዋን፣ ቶቤልና ሜሼኽ ከአንቺ ጋራ ይነግዱ ነበር፤ ባሪያዎችንና የናስ ዕቃዎችን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።
“ ‘ከሀብት ከንብረትሽ ብዛት የተነሣ፣ ደማስቆ የኬልቦንን የወይን ጠጅና፣ የዛሐርን የበግ ጠጕር በማቅረብ ከአንቺ ጋራ ተገበያይታለች።
“ ‘ድዳን ግላስ በማቅረብ ከአንቺ ጋራ ትነግድ ነበር።
ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሯት፤ ቀድሞ ግን ስሟ ላይሽ ይባል ነበር።