ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤ እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ። ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ።
ፈርዖን ኒካዑ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ እግር አነገሠው፤ ኤልያቄም የተባለ ስሙንም ለውጦ ኢዮአቄም አለው። ነገር ግን ኢዮአካዝን በምርኮ ወደ ግብጽ ወሰደው፤ እርሱም በዚያ ሞተ።
እንዲህም በል፤ “ ‘እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴት ያለች አንበሳ ነበረች! በደቦል አንበሶች መካከል ተጋደመች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።
አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤ በጕድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤ እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።
እርሱም በአንበሶች መካከል ተጐማለለ፤ እየበረታም ሄደ፤ ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ።
መሳፍንቷ እያገሣ ግዳዩን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ በውስጧ ያሤራሉ፤ ሕዝቡን ይበላሉ፤ ንብረትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ፤ ብዙዎችንም ሴቶች መበለት ያደርጋሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ “ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣ በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤ በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።
የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!
ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦ “ዳን ከባሳን ዘልሎ የሚወጣ፣ የአንበሳ ደቦል ነው።”