እንዲህም በል፤ “ ‘እናትህ በአንበሶች መካከል እንዴት ያለች አንበሳ ነበረች! በደቦል አንበሶች መካከል ተጋደመች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች።
ብርቱው አንበሳ ዐደን በማጣት ይሞታል፤ የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ!
ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።
“ስለ እስራኤል መሳፍንት ሙሾ አውጣ፤
ከግልገሎቿ መካከል አንዱን አሳደገችው፤ እርሱም ብርቱ አንበሳ ሆነ። ግዳይ መንጠቅን ተማረ፤ ሰዎችንም በላ።
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብጽ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤ “ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣ በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤ በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።
የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ ክብራቸው ተገፍፏልና፤ የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!
ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦ “ዳን ከባሳን ዘልሎ የሚወጣ፣ የአንበሳ ደቦል ነው።”