የምስክሩ ታቦት፣ ከመሎጊያዎቹና ከስርየት መክደኛው ጋራ፤
“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራለት።
ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ የተሠራ መደረቢያ፣ የለፋ የአቆስጣ ቈዳ መደረቢያና መከለያ መጋረጃ፤
ጠረጴዛውን ከነመሎጊያዎቹ ዕቃዎቹን ሁሉና ከገጸ ኅብስቱ ጋራ፤
በታቦቱም ላይ የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ አሁን ግን ስለ እነዚህ ነገሮች በዝርዝር መናገር አንችልም።
የመጀመሪያዪቱ ድንኳን ቆማ እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።