ቀይ ከተነከረ የአውራ በግ ቈዳ የተሠራ መደረቢያ፣ የለፋ የአቆስጣ ቈዳ መደረቢያና መከለያ መጋረጃ፤
ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤
ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቈዳ ይሁን።
ከዚያም የማደሪያውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡት፦ እነዚህም ድንኳንና ዕቃዎቹ ሁሉ፣ ማያያዣዎችን፣ ክፈፎችን፣ አግዳሚዎችን፣ ቋሚዎችንና መሠረቶችን፤
የምስክሩ ታቦት፣ ከመሎጊያዎቹና ከስርየት መክደኛው ጋራ፤