መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርተው በንሓስ ለበጧቸው።
ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤
ለመብራት የወይራ ዘይት፤ ለቅብዐ ዘይቱና ለጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፤
ለናሱ ፍርግርግ ማንደጃ አራት ማእዘኖች መሎጊያዎቹን እንዲይዙ የንሓስ ቀለበቶችን ሠሩ።
መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጐኖች ይሆኑ ዘንድ መሎጊያዎቹን በቀለበቶቹ ውስጥ አስገቧቸው፤ ውስጡንም ክፍት በማድረግ ከሳንቃዎች ሠሩት።
ስለዚህ ከግራር ዕንጨት ታቦት ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረጽሁ፤ ሁለቱንም ጽላት በእጆቼ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።