ለናሱ ፍርግርግ ማንደጃ አራት ማእዘኖች መሎጊያዎቹን እንዲይዙ የንሓስ ቀለበቶችን ሠሩ።
ጠረጴዛውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች ይይዙ ዘንድ፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ አጠገብ ይሁኑ።
ዐመድ ማውረጃ የሚሆን እንደ መረብ የሆነ የንሓስ ፍርግርግ አድርግለት በአራቱም የመረብ ማእዘኖች ላይ የንሓስ ቀለበቶች አብጅ።
ለመሠዊያውም ከጠርዝ በታች ሆኖ ከመሠዊያው ግማሽ ቁመት ላይ የሚሆን የንሓስ ፍርግርግ ማንደጃ ሠሩ።
መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርተው በንሓስ ለበጧቸው።