ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።
ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ።
“ለአደባባዩ መግቢያ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ያሉት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከቀጭን በፍታ የተፈተለ፣ ጥልፍ ጠላፊ የጠለፈበት ሃያ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይሁን።