ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ።
“ለድንኳኑ ደጃፍ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ዐዋቂ የተጠለፈ መጋረጃ አብጅ።
በምሥራቅ ጫፍ በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው አደባባይ አሁንም ዐምስት ክንድ ስፋት ይኑረው።
ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።
“ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣
ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋራ ርዝመታቸው ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው መግቢያ ላይ ነበሩ፤