ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣ ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።
ሸንጋይ አንደበት ካለው ይልቅ፣ ሰውን የሚገሥጽ ውሎ ዐድሮ ይወደዳል።
ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለሞገስ ነው፤ ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤
የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣ የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል።
አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።
ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”
ይህን ከተናገረ በኋላም ጉባኤው እንዲበተን አደረገ።
የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።