ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቋል፤ ቃሉም አልተሰማም።
የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።
ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤ መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።
ጠቢብ ሰው ታላቅ ኀይል አለው፤ ዕውቀት ያለውም ሰው ብርታትን ይጨምራል፤
ምክርና ትክክለኛ ጥበብ የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ።
መጥረቢያ ቢደንዝ፣ ጫፉም ባይሳል፣ ብዙ ጕልበት ይጨርሳል፤ ብልኀት ግን ለውጤት ያበቃል።
ገንዘብ ጥላ ከለላ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ጥበብም ጥላ ከለላ ነው፤ የዕውቀት ብልጫዋ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት መጠበቋ ነው።
በአንድ ከተማ ካሉ ዐሥር ገዦች ይልቅ፣ ጥበብ ጠቢቡን ሰው ኀያል ታደርገዋለች።
ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤ ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።