ወንዞች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ባሕሩ ግን ፈጽሞ አይሞላም፤ ወንዞች ወደ መጡበት ስፍራ፣ ወደዚያ እንደ ገና ይመለሳሉ።
ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ ዞሮ ዞሮ ይሄዳል፤ ዘወትርም ወደ ዑደቱ ይመለሳል።
ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ ጆሮም በመስማት አይሞላም።