ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ፦ “ዛብሎን ሆይ፤ ወደ ውጭ በመውጣትህ፣ አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ፤
ልያም፣ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ክሶኛል” አለች፤ ስሙንም ይሳኮር ብላ አወጣችለት።
ወደ ምዕራብም በመሄድ በመርዓላ በኩል ያልፋል፤ ደባሼትን ተጠግቶም በዮቅንዓም አጠገብ እስካለው ወንዝ ድረስ ይዘልቃል።
መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶች ከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋራ ነበር፤ የጦር አዛዦች ከማኪር፣ የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።