በግርማው እንደ በኵር ኰርማ ነው፤ ቀንዶቹም የጐሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን፣ በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም ዐሥር ሺሕዎቹ ናቸው፤ የምናሴም ሺሕዎቹ እንደዚሁ ናቸው።”
አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፤ ልጄ ዐውቃለሁ፤ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እንቢ አለው።
በዚህ ጊዜ፣ የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እስኪጠፉ ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’ ” አለ።
ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች፤ እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።
ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤ በእነርሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቷል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።
ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከርሱ ቢሆንም፣ የብኵርና መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።
የምናሴ ነገድ እኩሌታ ሕዝብ ቍጥር ብዙ ነበረ፤ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣል አርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው።
ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።
ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ ሢርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤ በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።
ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴ የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤ በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ።
ጐሽ ዐብሯቸው፣ ኰርማም ከወይፈን ጋራ ይወድቃል፤ ምድራቸው በደም ትርሳለች፤ ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።
ደካሞቹን በጎች በጐናችሁና በትከሻችሁ ስለምትገፈትሩ፣ እስኪባረሩም ድረስ በቀንዳችሁ ስለምትወጓቸው፣
አውራ በጉም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲጐሽም አየሁ። ምንም ዐይነት እንስሳ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም ሊያድን የሚችል አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ አደረገ፤ ታላቅም ሆነ።
ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤ እስራኤልም ረክሳለች።
“ኤፍሬም ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፤ ምን ላድርግህ? ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ጉም፣ እንደሚጠፋም የጧት ጤዛ ነው።
እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣ የኤፍሬም ኀጢአት፣ የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።
እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው።
“እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው፤ ጠላቶች የሆኗቸውን ሕዝብ ያነክታሉ፤ ዐጥንቶቻቸውን ያደቅቃሉ፤ በፍላጾቻቸው ይወጓቸዋል።
እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ።
እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።
የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት።
ነገር ግን ደን የለበሰው ኰረብታማው አገር የእናንተ ነው፤ ሄዳችሁ መንጥሩት፣ ዳር ድንበሩ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ከነዓናውያን የብረት ሠረገላ ቢኖራቸውና ብርቱዎች ቢሆኑም እንኳ ከዚያ ታስወጧቸዋላችሁ።”
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህ ደስ ይለኛልና።