እግዚአብሔር ይህን አይቶ ናቃቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ ተቈጥቷልና።
ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ርስቱንም ተጸየፈ።
አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ ክፉም ከአንተ ጋራ አያድርም።
እግዚአብሔር ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ።
አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤ የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው።
ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።
“ወዳጄ፣ ከብዙዎች ጋራ ተንኰሏን እየሸረበች፣ በቤቴ ውስጥ ምን ጕዳይ አላት? ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ሊያስቀርልሽ ይችላልን? እነዚህንስ በመፈጸም፣ ደስተኛ መሆን ትችያለሽን?”
የዘበኞቹ አዛዥ ኤርምያስን ለብቻው ወስዶ፣ እንዲህ አለው፤ “አምላክህ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ጥፋት ተናገረ፤
ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤ መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን፣ ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤ በጽኑ ቍጣው፣ ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ።
ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም።
የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ። በጎቹ ጠሉኝ፤ እኔም፣ ሰለቸኋቸው፤
እንግዲህ ለብ ያልህ ብቻ እንጂ ትኵስ ወይም ቀዝቃዛ ስላልሆንህ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው።
እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው።