አባት የሆነህን ዐለት ከዳኸው፤ የወለደህን አምላክ ረሳኸው።
በግብጽ ታላቅ ነገር ያደረገውን፣ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ፤
እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።
ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።
አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤ መሸሸጊያ ዐለትህንም አላስታወስህም፤ ስለዚህ ምርጥ ተክል ብትተክልም፣ እንግዳ ዘርንም ብትዘራ፣
ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።
“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤ “እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣ ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን፣ እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።
እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት፣ መንገዳቸውን አጣመዋልና፣ የእስራኤል ሕዝብ ጩኸት፣ አሳዛኝ ልቅሶ ባድማ ከሆኑት ኰረብቶች ተሰማ።
በመካከልሽ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጕቦ ይቀበላሉ፤ አንቺም ዐራጣና ከፍተኛ ወለድ በመውሰድ ከባልንጀራሽ የማይገባ ትርፍ ዘረፍሽ፤ እኔንም ረስተሻል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ ቤተ መንግሥቶችንም ሠራ፤ ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አበዛ፤ እኔ ግን በከተሞቻቸው ላይ እሳትን እለቃለሁ፤ ምሽጎቻቸውንም ይበላል።”
ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።
እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።
ከባርነት ምድር ከግብጽ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ!
በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ።
ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብጽ ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን ትረሳለህ።
አምላክህን እግዚአብሔርን ብትረሳና ሌሎችን አማልክት ብትከተል፣ ብታመልክና ለእነርሱ ብትሰግድላቸው በርግጥ እንደምትጠፉ ዛሬ እመሰክርባችኋለሁ።
“እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱት፤ ስለዚህ ለአሦር የጦር አዛዥ ለሲሣራ፣ ለፍልስጥኤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ አሳልፎ ሸጣቸው።