ይህች መልእክት ከተነበበችላችሁ በኋላ በሎዶቅያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ደግሞ በሎዶቅያ ያለችውን መልእክት አንብቡ።
ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፤ “ባቢሎን በደረስህ ጊዜ፣ ይህን ቃል ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማንበብ አትዘንጋ።
ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ስለማያውቁ ሁሉ ምን ያህል እየተጋደልሁ እንደ ሆነ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤
ደግሞም ስለ እናንተ እንዲሁም በሎዶቅያና በኢያራ ከተሞች ስላሉት ተግቶ እንደሚሠራ እኔ እመሰክርለታለሁ።
በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች፣ ለንምፉን፣ በቤቷም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ይህ መልእክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ ዐደራ እላችኋለሁ።
በዚህ መልእክት ላይ ላለው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ እንደዚህ ያለውን ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት፤ በሥራውም እንዲያፍር ከርሱ ጋራ አትተባበሩ።