በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች፣ ለንምፉን፣ በቤቷም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
በእነርሱ ቤት ላለች ቤተ ክርስቲያንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ አገር ለመጀመሪያ ወደ ክርስቶስ ለተመለሰው፣ ለወዳጄ ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ምክንያቱም ታላቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ብዙ ተቃዋሚዎችም አሉብኝ።
ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ስለማያውቁ ሁሉ ምን ያህል እየተጋደልሁ እንደ ሆነ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤
ደግሞም ስለ እናንተ እንዲሁም በሎዶቅያና በኢያራ ከተሞች ስላሉት ተግቶ እንደሚሠራ እኔ እመሰክርለታለሁ።
ይህች መልእክት ከተነበበችላችሁ በኋላ በሎዶቅያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ደግሞ በሎዶቅያ ያለችውን መልእክት አንብቡ።
ለእኅታችን ለአፍብያ፣ ዐብሮን ወታደር ለሆነው ለአርክጳ፣ በቤትህም ላለችው ቤተ ክርስቲያን፤