ዐብሯቸውም ሄደ። ወደ ዮርዳኖስም ሄደው ዛፎች መቍረጥ ጀመሩ።
ከመካከላቸውም አንዱ፣ “አንተስ ከአገልጋዮችህ ጋራ አትመጣምን?” አለው። ኤልሳዕም፣ “ዕሺ እመጣለሁ” አለ፤
ከእነርሱም አንዱ ዛፍ እየቈረጠ ሳለ፣ መጥረቢያው በርሮ ከውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፣ “ወየው ጌታዬ፤ የተውሶ መጥረቢያ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ።
እነሆ፤ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋራ ዕንጨት ለመቍረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፣ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።
ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ዕንጨትህን እየፈለጡ፣ ውሃህንም እየቀዱ በሰፈርህ የሚኖሩ መጻተኞችም ዐብረውህ ቆመዋል።