ከመካከላቸውም አንዱ፣ “አንተስ ከአገልጋዮችህ ጋራ አትመጣምን?” አለው። ኤልሳዕም፣ “ዕሺ እመጣለሁ” አለ፤
የልጁ እናት ግን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፤ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፣ ፈጽሞ ትቼህ አልሄድም” አለችው፤ ስለዚህ ተነሥቶ ተከተላት።
ንዕማንም፣ “እባክህ፤ ሁለት መክሊት ውሰድ” በማለት ግያዝን አስጨንቆ ለመነው። ከዚያም ሁለቱን መክሊት ብር፣ በሁለት ከረጢት ውስጥ አስሮ ሁለት ሙሉ ልብስ ጨምሮ ለሁለት አገልጋዮቹ አስያዘ፤ እነርሱም ያን ተሸክመው ከግያዝ ፊት ፊት ሄዱ።
ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ሄደን፣ እያንዳንዳችን ምሰሶ ቈርጠን እናምጣ፣ በዚያም የምንቀመጥበትን መኖሪያ እንሥራ።” እርሱም፣ “ይሁን ሂዱ” አላቸው።
ዐብሯቸውም ሄደ። ወደ ዮርዳኖስም ሄደው ዛፎች መቍረጥ ጀመሩ።
“አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤ ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው፤ “ሀልዎትህ ከእኛ ጋራ ካልሄደ ከዚህ አትስደደን።
ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት ዐብረው ተቀመጡ። የልጅቷም አባት፣ “እባክህ ዛሬም እዚሁ ዐድረህ ተደሰት” አለው።
ባርቅም፣ “ዐብረሽኝ የምትሄጂ ከሆነ እሄዳለሁ፤ ዐብረሽኝ የማትሄጂ ከሆነ ግን አልሄድም” አላት።