Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ሳሙኤል 2:34

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያች ዕለት ያ የእግዚአብሔር ሰው፣ እንዲህ ሲል ምልክት ሰጠ፤ “እግዚአብሔር የሰጠውም ምልክት፣ ‘እነሆ፣ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በላዩም ላይ ያለው ዐመድ ይፈስሳል’ ” የሚል ነው።

“እንግዲህ አንቺም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ የምትኖሪበትን ከተማ እግርሽ እንደ ረገጠ፣ ልጁ ይሞታል፤

ይህ ምልክት ይሁናችሁ፤ ሕፃን ልጅ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።”

እነዚህ ምልክቶች በተፈጸሙ ጊዜ እጅህ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነውና።

ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው በዐጭር ይቀጫሉ።

በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በዔሊና በቤተ ሰቡ ላይ የተናገርሁትን ሁሉ እፈጽማለሁ።

የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ተገደሉ።

ወሬውን ያመጣውም ሰው፣ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሰራዊቱም ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት።

የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፣ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፣ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ አለችው።

ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” አለች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች