ከመሠዊያዬ የማላስወግዳቸው ዘሮችህ በሕይወት የሚተርፉትም ዐይኖችህን በእንባ ለማፍዘዝ፣ ልብህን በሐዘን ለማደንዘዝ ብቻ ነው፣ ሌሎቹ ዘሮችህ ግን በሙሉ በለጋነታቸው በዐጭር ይቀጫሉ።
እርሱ በሬዎችን፣ ኰርማዎችንና በጎችን በብዛት ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሰራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጠርቷል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም።
አዶንያስ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋራ ተመካከረ፤ እነርሱም ድጋፋቸውን ሰጡት።
እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
በማደሪያዬም መከራ ታያለህ፤ ምንም እንኳ ለእስራኤል በጎ ነገር ቢደረግም፣ በቤተ ሰብህ ውስጥ ሽማግሌ ፈጽሞ አይገኝም።
“ ‘በሁለቱ ልጆችህ በአፍኒንና በፊንሐስ ላይ የሚደርሰው ላንተ ምልክት ይሆንሃል፣ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።
ንጉሡም ዶይቅን፣ “እንግዲያውስ አንተው ዙርና ካህናቱን ግደላቸው” ብሎ አዘዘው። ኤዶማዊው ዶይቅም ዞረና ገደላቸው። በዚያች ዕለት ሰማንያ ዐምስት የበፍታ ኤፉድ የለበሱ ካህናትን ገደለ።