የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፣ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር።
ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢብኖብ የተባለ፣ የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ፤ እርሱም ዳዊትን ለመግደል ዐሰበ።
ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ በተደረገ ሌላ ጦርነትም፣ የቤተ ልሔሙ የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን፣ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጋት ሰው የጎልያድን ወንድም ገደለው።
ደግሞም ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብጻዊ ገደለ፤ ግብጻዊው የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር በእጁ ቢይዝም፣ በናያስ ግን ቈመጥ ይዞ ገጠመው፤ ከግብጻዊው እጅ ጦሩን ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ፤ የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጋት ሰው የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።
ፍልስጥኤማዊውም፣ ጋሻ ጃግሬውን እፊት እፊቱ በማስቀደም፣ ወደ ዳዊት እየቀረበ መጣ።