በእግሮቹ ላይ የናስ ገምባሌ አድርጎ፣ በጫንቃው ላይ ደግሞ የናስ ጭሬ ይዞ ነበር።
ንጉሥ ሰሎሞን ከጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር።
ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ከጥፍጥፍ ወርቅ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፣ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሰራዊት ጌታ በሆነው፣ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
እርሱም ከናስ የተሠራ የራስ ቍር ደፍቶ፣ ክብደቱ ዐምስት ሺሕ ሰቅል የሆነ የናስ ጥሩር ለብሶ ነበር።