ሳፊምና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው።
የብንያም ልጆች፦ ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣ አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌን ሑፊምና አርድ ናቸው።
እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው።
የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው።
ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር። ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣
ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።