እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺሕ ተዋጊዎች ነበሯቸው።
የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን። የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳአር፤
ሳፊምና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው።