እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ጌዶር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።
የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ።
አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የሦኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ። የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤
ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሑር ዘሮች ናቸው።
በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፣ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነባት ነበረች። በቀድሞ ዘመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮች ናቸው።
የዳቤር ንጉሥ፣ አንድ የጌድር ንጉሥ፣ አንድ
ሐልሑል፣ ቤትጹር፣ ጌዶር፣