እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጐሣቸው መሪዎች ነበሩ። የየቤተ ሰባቸውም ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤
የእግዚአብሔርም ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።
የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ።
እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ጌዶር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።
የየቤተ ሰቡም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤል፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች፣ የታወቁ ሰዎችና የየቤተ ሰባቸው አለቆች ነበሩ።