ሰሜኢ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ ጐሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።
የማስማዕ ዘሮች፤ ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዛኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።
የኖሩባቸውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ቤርሳቤህ፣ ሞላዳ፣ ሐጻርሹዓል፣
የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ ዘጠኝ ሺሕ ሦስት መቶ ነው።
የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ነው።
እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ።
እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።