የማስማዕ ዘሮች፤ ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዛኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።
ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።
ሰሜኢ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ ጐሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።