Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ዜና መዋዕል 28:6

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አለኝ፤ ‘ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጬዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፣ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ለስሜ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ ከአንተ ቀጥሎ በዙፋንህ የማስቀምጠው ልጅህ ነው’ ብሎ እንደ ነገረው፣ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ ለመሥራት ዐስቤአለሁ።

“እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጽሟል፤ እኔም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ።

አሁን እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ያነገሥኸኝ ብዛቱ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ሕዝብ ላይ ስለ ሆነ፣ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና።

በመግቢያው በር ዙሪያ ባሉት ወጣ ወጣ ባሉት ግንቦች ሁሉ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ለካ፤ ስድሳ ክንድም ነበር። የተለካውም ከአደባባዩ ፊት ለፊት እስካለው መተላለፊያ በረንዳ ድረስ ነበር።

ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቷል።

ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።

ቀደም ባለው ክፍል ደግሞ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች