እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂና፣ ‘ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ “ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል” ብለህ ለእኔ ለአገልጋይህ አልማልህልኝም ነበር? ታዲያ አዶንያስ የነገሠው ስለ ምንድን ነው?’ በዪው፤
ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ከአንተ ቀጥሎ በጌታዬ በንጉሡ ዙፋን ላይ ማን መቀመጥ እንዳለበት እንድታሳውቀው የእስራኤል ዐይን ሁሉ አንተን ይመለከታል።
‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በእኔም ምትክ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር የማልሁልሽን ዛሬ በእውነት እፈጽማለሁ።”
አጅባችሁት ወደ ላይ ውጡ፤ ከዚያም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ፤ በእኔም ምትክ ይግዛ፤ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ሾሜዋለሁ።”
እርሱም፣ “መንግሥቱ የእኔ እንደ ነበረና እስራኤልም ሁሉ እኔ እንድነግሥ ዐይናቸውን ጥለውብኝ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂአለሽ፤ ሆኖም ነገሩ ከእግዚአብሔር የተቈረጠለት ሆነና ሁኔታዎች ተለዋውጠው፣ መንግሥቱ ለወንድሜ ተላለፈ።
“እግዚአብሔርም የተናገረውን ቃል ፈጽሟል፤ እኔም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በአባቴ በዳዊት እግር ተተክቼ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ ተቀምጫለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም ስም ቤተ መቅደስ ሠርቻለሁ።
በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም አኖረዋለሁ፤ ዙፋኑም ለዘላለም ይጸናል።’ ”
ዳዊት በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።
ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር አምላክ በመሆኑ፣ ሥራው ከባድ ነው።
ሰሎሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።
ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጐድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ልጁ ሰሎሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
በአንተ ደስ ተሰኝቶ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ፣ በዙፋኑ ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ ለእስራኤል ካለው ፍቅርና ለዘላለም ሊያጸናቸው ካለው ፍላጎት የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን ታደርግ ዘንድ አንተን በላያቸው ላይ አንግሦሃል።”
አምላክህ እግዚአብሔር የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፤ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ፣ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ።