የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሾብዓም የጦር መኰንኖቹ አለቃ ነበረ፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም ይህ ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሴብ በሴትቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፣ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው የገደለ ነው።
ከዚያም መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “ዳዊት ሆይ፤ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፤ እኛ ከአንተ ጋራ ነን፤ ሰላም ፍጹም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤ አምላክህ ይረዳሃልና።” ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ የሰራዊቱም አለቃ አደረጋቸው።
በመጀመሪያው ወር፣ የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺሕ ሰዎች ነበሩ።