የዳዊት ኀያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱ በምድሪቱ ሁሉ ትሰፋ ዘንድ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
ከዚያም አበኔር ዳዊትን፤ “ከአንተ ጋራ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፣ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ሄጄ፣ ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።
ስለዚህ የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን ገባ። እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በተናገረው መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ስለ ነበሩ፣ አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።
እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፣ የሳኦልን መንግሥት አንሥተው ለርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደሚገኝበት ወደ ኬብሮን የመጡት ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤
ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺሕ ስምንት መቶ፤
እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው። ወደ ኬብሮን የመጡትም ዳዊትን በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው። የቀሩትም እስራኤላውያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።
የሚያስፈልጋቸውንም ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ስለ ነበር፣ ሰዎቹ እየበሉና እየጠጡ ከዳዊት ጋራ ሦስት ቀን ቈዩ።
የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።
ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የከፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሡና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኀላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኀያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።
እግዚአብሔር ሳሙኤልን፣ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተ ልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፣ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።