Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


112 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ጭንቀትን ለማስወገድ

112 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ጭንቀትን ለማስወገድ

በችግርና በመከራ ጊዜ፣ ስሜታችን ያጥለቀልቅነና የእግዚአብሔርን ተስፋዎች ልንረሳ እንችላለን። ግን እንደዚህ ባሉ እርግጠኛ ባልሆኑ ጊዜያት፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንዳለና ሁሉንም ነገር እንደሚቆጣጠር እናስታውስ።

በአምላካችን ቸርነት አንጠራጠር፣ ነገር ግን በፍቅሩና በእንክብካቤው እንመካ። አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም፣ በእሱ ጥበቃ ውስጥ መጠጊያ ማግኘት እንችላለን። እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቶልናል።

«ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።» (ማቴዎስ 28:20)።


መዝሙር 46:1

አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 42:11

ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፣ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ናሆም 1:7

እግዚአብሔር መልካም ነው፤ በጭንቅ ጊዜም መሸሸጊያ ነው። ለሚታመኑበት ይጠነቀቅላቸዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 118:5

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 9:9

እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:17

በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 31:6

ብርቱና ደፋር ሁኑ፤ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡላቸው። አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሄዳልና፤ አይተውህም፤ አይጥልህምም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:6-7

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢያሱ 1:9

በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢያሱ 1:5

በሕይወት በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበርሁ ሁሉ ከአንተም ጋራ እሆናለሁ፤ ከቶ አልጥልህም፤ አልተውህም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 18:6

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም በፊቱ ከጆሮው ደረሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:35

ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ራብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ፣ ወይስ ሰይፍ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:16

እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:19

የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 22:24

እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣ አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤ ፊቱንም ከርሱ አልሰወረም፤ ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:19

የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:6

ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:1-4

በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤ በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል። በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ። “ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ። ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ። ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።” እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ። እርሱ ከዐዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 23:4

በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 17:7-8

“ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚታመን፣ መታመኛውም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውሃ ዳር እንደ ተተከለ፣ ሥሩንም ወደ ወንዝ እንደ ሰደደ ዛፍ ነው፣ ሙቀት ሲመጣ አይፈራም፤ ቅጠሉም ዘወትር እንደ ለመለመ ነው፤ በድርቅ ዘመን አይሠጋም፤ ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:25

ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤ መልካም ቃል ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:17

የልቤ መከራ በዝቷል፤ ከጭንቀቴ ገላግለኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 27:5

በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በተቀደሰ ድንኳኑም ውስጥ ይሸሽገኛል፤ በዐለቱ ላይ ከፍ ያደርገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 30:10

እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ነህምያ 8:10

ነህምያም፣ “ሂዱ፤ ጥሩ ምግብ በመብላት፣ ጣፋጩን በመጠጣት ደስ ይበላችሁ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ካላችሁ ላይ ከፍላችሁ ላኩላቸው። ይህች ቀን ለጌታችን የተቀደሰች ናት፤ የእግዚአብሔር ደስታ ብርታታችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕንባቆም 3:17-18

ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 31:7

በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ መከራዬን አይተሃልና፤ የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:4

እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:17-18

ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:39-40

የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም፤ ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤ እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 40:1-2

እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ። ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን፣ ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አትንፈገኝ፤ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፤ ስፍር ቍጥር የሌለው ክፋት ከብቦኛልና፤ የኀጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዝቷል፤ ልቤም ከድቶኛል። እግዚአብሔር ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፤ ጕዳቴንም የሚሹ፣ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ። በእኔ ላይ፣ “ዕሠይ! ዕሠይ!” የሚሉ፣ በራሳቸው ዕፍረት ይደንግጡ። አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስ ይበላቸው፤ ዘወትር የአንተን ማዳን የሚወድዱ፣ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ። እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ ጌታ ግን ያስብልኛል። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬም ነህና፤ አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ። ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 42:5

ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ አዳኜና አምላኬን ገና አመሰግነዋለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 55:22

የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 56:3

ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 57:1

ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤ ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤ በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 61:2-3

ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ። አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 62:1-2

ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከርሱ ዘንድ ነው። በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ። እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤ ኀይል የእግዚአብሔር ነው። ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤ አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ። ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 69:29

ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 71:20-21

ብዙ መከራና ጭንቅ ብታሳየኝም፣ ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፤ ከምድር ጥልቅም፣ እንደ ገና ታወጣኛለህ። ክብሬን ትጨምራለህ፤ ተመልሰህም ታጽናናኛለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:26

ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 86:7

አንተ ስለምትመልስልኝ፣ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 88:1-3

አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ። ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን? የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን? ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን? እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤ መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ። ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ። ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ በአንድነትም ዙሪያዬን ዐጥረው ያዙኝ። ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ። ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል። ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:1-2

በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። ክፉ ነገር አያገኝህም፤ መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤ በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል። በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ። “ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ። ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ። ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።” እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:15

ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 102:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ። ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል። አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ ለዐፈሯም ይሳሳሉ። ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣ የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ። እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል። እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤ “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤ ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤ በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 107:6

በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 118:5-6

በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:50

ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣ ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:92

ሕግህ ደስታዬ ባይሆን ኖሮ፣ በመከራዬ ወቅት በጠፋሁ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:143

መከራና ሥቃይ ደርሶብኛል፤ ነገር ግን ትእዛዝህ ደስታዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 121:1-2

ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል? ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 138:7

በመከራ መካከል ብሄድም፣ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 142:3

መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣ መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤ በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣ ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 143:7-8

እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈጥነህ መልስልኝ፤ መንፈሴ ደከመች፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር። በአንተ ታምኛለሁና፣ በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና፣ የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:5-6

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 18:10

የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:10

በመከራ ጊዜ ፈራ ተባ ካልህ፣ ዐቅምህ ምንኛ ደካማ ነው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 25:4

ለድኻ መጠጊያ፣ በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ ከማዕበል መሸሸጊያ፣ ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል። የጨካኞች እስትንፋስ፣ ከግድግዳ ጋራ እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:3

በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 35:4

የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤ “በርቱ፤ አትፍሩ፤ አምላካችሁ ይመጣል፤ ሊበቀል ይመጣል፤ እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ ሊያድናችሁ ይመጣል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:29-31

ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጕልበት ይጨምራል። የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “በምድረ በዳ የጌታን መንገድ፣ አዘጋጁ፤ ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣ በበረሓ አስተካክሉ። ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፤ ይታክታሉም፤ ጐበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ። እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:13

እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:2

በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 49:13

ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 51:12

“የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ ሟች የሆኑትን ሰዎች፣ እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆች ለምን ትፈራለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:10

ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 1:8

እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራቸው” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 29:11

ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጣችሁ፣ የሰላም ሐሳብ እንጂ ለክፉ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:22-23

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:31-33

ጌታ ሰውን፣ ለዘላለም አይጥልምና፤ መከራን ቢያመጣ እንኳ ይራራል፤ ታላቅ ፍቅሩ አይለወጥምና። ሆነ ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:57

በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣ እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:16

የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትንም እመልሳለሁ። የተጐዱትን እጠግናለሁ፤ የደከሙትንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን ግን አጠፋለሁ። መንጋውን በፍትሕ እጠብቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:4

የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:34

ስለዚህ ለነገ በማሰብ አትጨነቁ፤ የነገ ጭንቀት ለነገ ይደር፤ እያንዳንዱ ዕለት የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:28-30

“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ “ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ። ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:38

ከዚያም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ ዐዝናለች፤ እዚሁ ሁኑና ከእኔ ጋራ ነቅታችሁ ቈዩ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:22-26

ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን? ለመሆኑ፣ ከእናንተ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ሰዓት መጨመር የሚችል ማን ነው? እንግዲህ ቀላሉን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ፣ ስለ ሌላው ነገር ለምን ትጨነቃላችሁ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:1

“ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:27

ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 16:33

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:3-5

በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤ ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:18

የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው፣ ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋራ ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:26-27

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል። ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:28

እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:35-39

ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው? ችግር ነው ወይስ ሥቃይ፣ ወይስ ስደት፣ ወይስ ራብ፣ ወይስ ዕራቍትነት፣ ወይስ አደጋ፣ ወይስ ሰይፍ? ይህም፣ “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቈጥረናል” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:3-4

የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:8-9

ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:16-18

ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየጠፋ ቢሄድም እንኳ፣ ውስጣዊው ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፤ ምክንያቱም ቀላልና ጊዜያዊ የሆነው መከራችን ወደር የማይገኝለት ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል። ስለዚህ ዐይናችን የሚያተኵረው በሚታየው ነገር ላይ ሳይሆን በማይታየው ላይ ነው፤ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:13

ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 1:11

ታላቅ ጽናትና ትዕግሥት ይኖራችሁ ዘንድ፣ እንደ ክቡር ጕልበቱ መጠን በኀይል ሁሉ እየበረታችሁ፣ ደስ እየተሰኛችሁ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ተሰሎንቄ 5:16-18

ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በማናቸውም ሁኔታ አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ተሰሎንቄ 3:3

ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱም ያበረታችኋል፤ ከክፉውም ይጠብቃችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር፣ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 4:15-16

በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:5-6

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል። ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:2-4

ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና። ስለዚህ ርኩሰትንና ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ክፋትን አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን፣ በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ። ቃሉ የሚናገረውን አድርጉ እንጂ ሰሚዎች ብቻ ሆናችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። ቃሉን የሚሰማ፣ ነገር ግን የሚለውን የማይፈጽም ሰው ፊቱን በመስተዋት እንደሚያይ ሰው ነው፤ ራሱንም አይቶ ይሄዳል፤ ወዲያውም ምን እንደሚመስል ይረሳል፤ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ ተመልክቶ የሚጸና፣ የሰማውን የሚያደርግና የማይረሳ ሰው በሥራው ብሩክ ይሆናል። አንደበቱን ሳይገታ፣ ልቡን እያሳተ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚል ሰው፣ ራሱን ያታልላል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው። በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆችና ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳትና ከዓለም ርኩሰት ራስን መጠበቅ ነው። ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ። ምንም የማይጐድላችሁ ፍጹማንና ምሉኣን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን ይፈጽም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:6-7

አሁን በብዙ ዐይነት ፈተና ውስጥ ሆናችሁ ለጥቂት ጊዜ መከራን ብትቀበሉም እንኳ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል። እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ፣ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጥና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:14

ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራ ቢደርስባችሁ ብፁዓን ናችሁ፤ “ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:12-13

ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ በመቀበላችሁ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:7

እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በርሱ ላይ ጣሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 4:18

በፍቅር ፍርሀት የለም፤ ፍጹም ፍቅር ግን ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሀት ከቅጣት ጋራ የተያያዘ ነውና። የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 3:10

በትዕግሥት እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ፣ እኔ ደግሞ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 7:16-17

ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከዚህም በኋላ አይጠሙም፤ ፀሓይ አይመታቸውም፤ ሐሩሩም ሁሉ አያቃጥላቸውም፤ ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 21:4

እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፏልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:13

እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣ እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 46:10

“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:18

ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 57:18-19

መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እመልሳለሁ፤ በእስራኤል አልቃሾች ከንፈር ላይ ምስጋና እፈጥራለሁ። በቅርብና በሩቅ ላሉት ሰላም፣ ሰላም ይሁን፤ እኔ እፈውሳቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ሳሙኤል 22:7

“በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ወደ አምላኬም ጮኽሁ። እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከጆሮው ደረሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

አንተ ብቻ ነህ ሁሉን ቻይ የሆንክ ጌታ፤ ልዑል ስምህንና ኃይልህን አወድሳለሁ። አንተን የሚመስልህ እንደሌለ፣ ከአንተም ጋር የሚወዳደር እንደሌለ አውቃለሁ። የሰማይ አምላኬ ሆይ፤ አንተ ለማንኛውም ችግር፣ ለቤተሰብ፣ ለገንዘብ ወይም ለጤና ችግር መፍትሔ ብቻ ሳትሆን፣ ራሱ መፍትሔው እንደሆንክ ተረድቻለሁና ወደ አንተ እጮኻለሁ። ተስፋዬን በአንተ ላይ አድርጌ በየቀኑ በቃል ኪዳንህ እንድጸና እርዳኝ። በመከራ ጊዜም ቢሆን እንደምትጠብቀኝ እርግጠኛ እንድሆን እርዳኝ፤ ምክንያቱም በፊትህ ከመሆን የበለጠ አስተማማኝ ቦታ የለም። አሁን ሸክሜን፣ ጭንቀቴን ሁሉ አንተ ዘንድ አኖራለሁ። ሀሳቤን፣ ስሜቴንና አቋሜን መንፈስ ቅዱስህ ይቆጣጠርልኝ፤ ለፈቃድህም ይገዛልኝ። ጌታ ሆይ፤ የሕይወትን ፈተናዎች በድፍረት እንዳሳልፍ ኃይል ስጠኝ። ልክ እንደ ኢዮብ በመከራው ልጆቹን፣ ንብረቱንና ጤንነቱን ቢያጣም በአንተ ላይ ያለውን እምነት እንዳላጣ፣ እኔም በየትኛውም ቦታ ከእኔ ጋር እንደምትሆን እምነቴን ሳላጣ ጸንቼ እንድቆም እርዳኝ። ስሜቴንና ፈቃዴን አንተ እንድትመራኝ በእጅህ አደርጋለሁ። ከጭንቀትና ከሸክም ሁሉ ነጻ እሆናለሁ። የክርስቶስን ደም በአእምሮዬ ላይ እጠራለሁ፤ የጠላትንም ውሸት ሁሉ እቃወማለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች