ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ዳዊት፥ “በእግዚአብሔር አመንሁ፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል” ብሎ እንደ ተናገረ በእግዚአብሔር በሚያምኑ ሰዎች ግን ፍርሀትና ድንጋጤ የለባቸውም። 2 ዳግመኛም አለ፥ “አርበኞች ቢከቡኝ፥ እኔ በእርሱ አመንሁ፤ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፤ እርስዋንም እፈልጋለሁ፥ በእርሱም ያመነ ለዘለዓለሙ በሕይወት ይኖራል፥ ከክፉ ነገርም የተነሣ አይፈራም።” 3 በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ሰው ማን ነው? ጠርቶትስ ቸል ያለው ማን ነው? 4 “የወደደኝን እወደዋለሁ፤ ያከበረኝንም አከብረዋለሁ፤ ወደ እኔ የተመለሰውንም እጠብቀዋለሁ” ብሏልና እርሱን ተስፋ አድርጎ ያፈረ ሰው ማን ነው? 5 የባልቴቲቱን ሰውነት አድኑ፤ በክፉ ነገር ከሚቃወማችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ያድናችሁ ዘንድ አድኗቸው፤ ጠብቋቸውም፤ ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁን ያድናቸዋል፤ የጻድቃን ልጆች ይባረካሉና፤ አትርፈውም ይሰጣሉ እንጂ እህልን አይቸገሩም። |