Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሶፎንያስ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩ፣ ተስማምተው እንዲያገለግሉት፣ አንደበታቸውን አጠራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚያን ጊዜም ሁሉም የጌታን ሥም እንዲጠሩና በአንድ ትከሻ እንዲያገለግሉት፥ ለሕዝቦች ንጹሕን አንደበት እመልስላቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “በዚያን ጊዜ ሕዝቦች ንጹሕ ንግግር እንዲናገሩ አደርጋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ሁሉም የእኔን የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩና በአንድነት እንዲያገለግሉኝ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሶፎንያስ 3:9
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዓ​ለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግ​ግ​ሩም አንድ ነበረ።


ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙ​ንም ሄኖስ አለው፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት የጀ​መረ ነው።


ባሕር አየች፥ ሸሸ​ችም፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ወደ​ኋ​ላው ተመ​ለሰ።


በዚያ ቀን አም​ስት የግ​ብፅ ከተ​ሞች በከ​ነ​ዓን ቋንቋ ይና​ገ​ራሉ፤ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይጠሩ ዘንድ ከተ​ሞች አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም አን​ዲቱ የጽ​ድቅ ከተማ ተብላ ትጠ​ራ​ለች።


በሩ​ቅም በቅ​ር​ብም ላሉ በሰ​ላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አፌ​ንም ዳሰ​ሰ​በ​ትና፥ “እነሆ፥ ይህ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህን ነክ​ቶ​አል፤ በደ​ል​ህም ከአ​ንተ ተወ​ገደ፤ ኀጢ​አ​ት​ህም ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለኝ።


ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ።


አንድ በት​ርም እን​ዲ​ሆኑ አን​ዱን ከሁ​ለ​ተ​ኛው ጋር ለአ​ንተ አጋ​ጥም፤ በእ​ጅ​ህም ውስጥ አንድ ይሁኑ።


ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።


መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች