Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሶፎንያስ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “የሞዓብን ስድብ፣ የአሞናውያንንም ፌዝ ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ በምድራቸውም ላይ ዝተዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ፤ በሕዝቤም ላይ አላግጠዋል፥ በድንበራቸውም ላይ ኮርተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞአብን ሕዝብ ፌዝና የአሞንን ሕዝብ ስድብ ሰምቼአለሁ፤ እነርሱም እንዴት አድርገው እንዳፌዙባቸውና ርስታቸውንም ለመውሰድ እንደ ዛቱባቸው ዐውቄአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሶፎንያስ 2:8
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።


ታና​ሺ​ቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም የወ​ገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም እስከ ዛሬ የአ​ሞ​ና​ው​ያን አባት ነው።


ስለ ሞዓብ የተ​ነ​ገረ ቃል። ሞዓብ በሌ​ሊት ትጠ​ፋ​ለች፤ የሞ​ዓ​ብም ምሽግ በሌ​ሊት ይፈ​ር​ሳል።


የሞ​ዓ​ብን ትዕ​ቢ​ትና እጅግ መኵ​ራ​ቱን ሰም​ተ​ናል፤ ትዕ​ቢ​ቱ​ንም አስ​ወ​ገ​ድሁ፤ ጥን​ቈ​ላህ እን​ዲህ አይ​ደ​ለ​ምና፥ እን​ዲ​ህም አይ​ደ​ለም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ያወ​ረ​ስ​ሁ​ትን ርስት ለሚ​ነ​ኩት ክፉ​ዎች ጎረ​ቤ​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ ከም​ድ​ራ​ቸው እነ​ቅ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እነ​ቅ​ለ​ዋ​ለሁ።


ስለ ሞአብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍ​ታ​ለ​ችና ወዮ​ላት! ቂር​ያ​ታ​ይም አፍ​ራ​ለች፤ ተይ​ዛ​ማ​ለች፤ መጠ​ጊ​ያ​ዋም አፍ​ራ​ለች፤ ደን​ግ​ጣ​ማ​ለች።


ስለ አሞን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሚል​ኮም ጋድን ይወ​ርስ ዘንድ ሕዝ​ቡም በከ​ተ​ሞቹ ላይ ይቀ​መጥ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሉ​ት​ምን? ወይስ ወራሽ የለ​ው​ምን?


ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጠላት በእ​ና​ንተ ላይ፦ እሰይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጥፋት፥ ለእኛ ርስት ሆነ​ዋል ብሎ​አ​ልና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ዳር​ቻ​ቸ​ውን ያሰፉ ዘንድ የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች ቀድ​ደ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአ​ሞን ልጆች ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ንጉሥ አጥ​ንት አመድ እስ​ኪ​ሆን ድረስ አቃ​ጥ​ሎ​ታ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የሞ​ዓብ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ዛሬ የግ​ብ​ፅን ተግ​ዳ​ሮት ከእ​ና​ንተ ላይ አስ​ወ​ግ​ጃ​ለሁ” አለው፤ ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌል​ገላ ተብሎ ተጠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች