Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከኦ​ሪት የተ​ነሣ ኀጢ​አት ስለ ታወ​ቀች ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሥር​ዐት በመ​ፈ​ጸም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አይ​ጸ​ድ​ቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሥጋ ለባሽ በርሱ ፊት ሊጸድቅ አይችልም፤ ይልቁንም በሕግ አማካይነት ኀጢአትን እንገነዘባለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 3:20
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ በቅ​ዱ​ሳኑ እንኳ አይ​ታ​መ​ንም፤ ሰማ​ይም በፊቱ ንጹሕ አይ​ደ​ለም።


ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም እስ​ራ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይታ​መ​ናል።


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


ከሁ​ሉም ይልቅ በሙሴ ሕግ መጽ​ደቅ የተ​ሳ​ና​ችሁ ናችሁ። በእ​ርሱ ግን ያመነ ሁሉ ይጸ​ድ​ቃል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።


ሰው የኦ​ሪ​ትን ሥራ ሳይ​ሠራ በእ​ም​ነት እን​ዲ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና።


አብ​ር​ሃም፥ ዘሩም ዓለ​ምን ይወ​ርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት አይ​ደ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እር​ሱ​ንም በማ​መን በእ​ው​ነ​ተና ሃይ​ማ​ኖቱ ይህን አገኘ እንጂ።


የኦ​ሪት ሕግ በአ​ፍ​ራሹ ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣ​ልና፤ የኦ​ሪት ሕግም ከሌለ መተ​ላ​ለፍ የለም።


ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢ​አት ምን እንደ ሆነች ሳት​ታ​ወቅ በዓ​ለም ውስጥ ነበ​ረች፤ ነገር ግን የኦ​ሪት ሕግ ገና ስላ​ል​መጣ ኀጢ​አት ተብላ አት​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


ኦሪ​ትስ ኀጢ​አ​ትን ታበ​ዛት ዘንድ መጣች፤ ኀጢ​አ​ትም ከበ​ዛች ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዛች።


ኀጢ​አት በዚ​ያች ትእ​ዛዝ ምክ​ን​ያት አሳ​ተ​ችኝ፤ በእ​ር​ሷም ገደ​ለ​ችኝ።


ይህስ ስለ​ምን ነው? ጽድ​ቃ​ቸው የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እንጂ በእ​ም​ነት ስለ አል​ሆነ ነው፤ የእ​ን​ቅ​ፋት ድን​ጋይ አሰ​ነ​ካ​ከ​ላ​ቸው።


የሞት መው​ጊያ ኀጢ​አት ናት፥ የኀ​ጢ​አ​ትም ኀይ​ልዋ ኦሪት ናት።


ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ እኛም የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ሳይ​ሆን በእ​ርሱ በማ​መ​ና​ችን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ነ​ናል፤ ሰው ሁሉ በኦ​ሪት ሥራ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና።


እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።


በኦ​ሪት ልት​ጸ​ድቁ የም​ት​ፈ​ልጉ እና​ንተ ከክ​ር​ስ​ቶስ ተለ​ይ​ታ​ችሁ ከጸ​ጋዉ ወድ​ቃ​ች​ኋል።


ኦሪት ምንም ግዳጅ አል​ፈ​ጸ​መ​ች​ምና፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ፋንታ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ን​ቀ​ር​ብ​በት ከእ​ር​ስዋ የሚ​ሻል ተስፋ ገብ​ቶ​አል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች