Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ውን ሕዝ​ቡን አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያስ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል በከ​ሰ​ሳ​ቸው ጊዜ መጽ​ሐፍ ያለ​ውን አታ​ው​ቁ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። ኤልያስ በእስራኤል ላይ ክስ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንዳቀረበ፣ መጽሐፍ ስለ እርሱ ምን እንደሚል አታውቁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝቡን አልጣላቸውም። ወይስ ኤልያስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እስራኤል እንዴት እንደተከራከረ መጽሐፍ ምን እንደሚል አታውቁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር አስቀድሞ የመረጠውን ሕዝብ አልጣለውም፤ ቅዱስ መጽሐፍ ስለ ኤልያስ ምን እንዳለ አታስታውሱምን? ደግሞስ ኤልያስ የእስራኤልን ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ምን ብሎ እንደ ከሰሰ አታውቁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 11:2
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።


ነገር ግን ብዙ ዓመ​ታት ታገ​ሥ​ሃ​ቸው፤ በነ​ቢ​ያ​ት​ህም እጅ በመ​ን​ፈ​ስህ መሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ አላ​ደ​መ​ጡም፤ ስለ​ዚ​ህም በም​ድር አሕ​ዛብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ሁሉ እን​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አለው፥ “ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው አት​መ​ል​ከት፤ እኔ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ችም ተመ​ኝቼ አል​ወ​ሰ​ድ​ሁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው አል​በ​ደ​ል​ሁም።”


ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔር ‘እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤’ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመ​ልቶ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ተመ​ለሰ፤ መን​ፈ​ስም ወደ ምድረ በዳ ወሰ​ደው።


ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ?


አሕ​ዛ​ብም ይህን ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አከ​በሩ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትም የተ​ዘ​ጋጁ ሁሉ አመኑ።


ከጥ​ንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የታ​ወቀ ነው።


“አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አለ​ቆ​ቻ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረጉ ይህን ባለ​ማ​ወቅ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት አው​ቃ​ለሁ።


አሮ​ን​ንም፦ ‘በፊት በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክ​ትን ሥራ​ልን፤ ያ ከም​ድረ ግብፅ ያወ​ጣን ሙሴ የሆ​ነ​ውን አና​ው​ቅ​ምና’ አሉት።


ለም​ት​ታ​ዘ​ዙ​ለት፥ እሺ ለም​ት​ሉ​ትም እና​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮች እንደ ሆና​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ለተ​ባ​በ​ራ​ች​ሁ​ለ​ትስ ራሳ​ች​ሁን እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ አታ​ው​ቁ​ምን? ኀጢ​አ​ት​ንም እሺ ብት​ሉ​አት፥ ተባ​ብ​ራ​ች​ሁም ብት​በ​ድሉ እና​ንት ለሞት ተገ​ዢ​ዎች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ጽድ​ቅ​ንም እሺ ብት​ሉ​አት ለበጎ ሥራም ብት​ተ​ባ​በሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናችሁ።


ዳግ​መ​ናም የክ​ብ​ሩን ባለ​ጠ​ግ​ነት ሊያ​ሳይ ቢወድ አስ​ቀ​ድሞ ለወ​ደ​ዳ​ቸ​ውና ለጠ​ራ​ቸው ለይ​ቅ​ርታ የተ​ዘ​ጋጁ የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክ​ትን ያመ​ጣል።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አይ​ታ​በ​ልም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን አይ​ደ​ሉ​ምና።


ቅዱ​ሳን ሰውን ሁሉ እን​ደ​ሚ​ዳኙ አታ​ው​ቁ​ምን? እና​ንተ ሰውን ሁሉ የም​ት​ዳኙ ከሆ​ና​ችሁ ይህን ትን​ሹን ነገር ልት​ዳኙ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ወድ ሰው ግን እርሱ በእ​ርሱ ዘንድ በእ​ው​ነት የታ​ወቀ ነው።


ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆ​ንም ምን እን​ደ​ም​መ​ርጥ አላ​ው​ቅም።


ከጥ​ንት ጀምሮ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብዙ ዐይ​ነ​ትና በብዙ ጎዳና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በነ​ቢ​ያት ተና​ገረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች