Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በኵር ሆኖ የቀረበው የቡሖው ክፍል ቅዱስ ከሆነ፣ ቡሖው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩ ቅዱስ ከሆነ፣ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በኩራቱም ቅዱስ ከሆነ ብኮው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከአንድ ዐይነት ሊጥ የመጀመሪያው ክፍል የተቀደሰ ከሆነ ሊጡ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ እንዲሁም የአንድ ዛፍ ሥሩ የተቀደሰ ከሆነ ቅርንጫፎቹም የተቀደሱ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በኵራቱም ቅዱስ ከሆነ ብሆው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 11:16
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃል ኪዳ​ኔ​ንም በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል፥ ከአ​ን​ተም በኋላ በዘ​ርህ መካ​ከል በት​ው​ል​ዳ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኪዳን አቆ​ማ​ለሁ፤ ለአ​ን​ተና ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ አም​ላክ እሆን ዘንድ።


የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።


በፊቴ ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። በእ​ር​ሻም የም​ት​ዘ​ራ​ትን የፍ​ሬ​ህን በኵ​ራት የመ​ከር በዓል፥ ዓመ​ቱም ሲያ​ልቅ ፍሬ​ህን ከእ​ርሻ ባከ​ማ​ቸህ ጊዜ የመ​ክ​ተ​ቻ​ውን በዓል ጠብቅ።


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ በኵ​ራት ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጣ። ጠቦ​ትን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።


እኔ የተ​መ​ረ​ጠች ወይን፥ ፍጹ​ምም እው​ነ​ተኛ ዘር አድ​ርጌ ተክ​ዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለ​ው​ጠሽ እን​ዴት መራራ የእ​ን​ግዳ ወይን ግንድ ሆንሽ?


የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ መከ​ሩ​ንም ባጨ​ዳ​ችሁ ጊዜ፥ የእ​ና​ን​ተን መከር በኵ​ራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤


ከቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ አን​ዳ​ን​ዶቹ ቢሰ​በሩ የዱር ወይራ የሆ​ንህ አን​ተን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእ​ነ​ር​ሱ​ንም ሥር​ነት አገ​ኘህ፤ እንደ እነ​ር​ሱም ዘይት ሆንኽ።


ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና።


የማ​ያ​ምን ባል በሚ​ስቱ ይቀ​ደ​ሳ​ልና፤ የማ​ታ​ምን ሚስ​ትም በባ​ልዋ ትቀ​ደ​ሳ​ለ​ችና፤ ያለ​ዚ​ያማ ልጆ​ቻ​ቸው ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ፤ አሁን ግን ቅዱ​ሳን ናቸው።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ አስ​ቀ​ድ​ሞም የተ​ሸ​ለ​ተ​ውን የበ​ግ​ህን ጠጕር ለእ​ርሱ ትሰ​ጣ​ለህ።


አሁ​ንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን የም​ድ​ሪ​ቱን ፍሬ ቀዳ​ም​ያት አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ።


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች