Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ስም​ህን የሚ​ወዱ ሁሉ በአ​ንተ ይታ​መ​ናሉ፥ አቤቱ፥ የሚ​ሹ​ህን አት​ተ​ዋ​ቸ​ው​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥ በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አምላክ ሆይ! በአንተ የሚተማመኑትን ሁሉ ስለማትተዋቸው ስምህን የሚያውቁ ሁሉ ይተማመኑብሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 9:10
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂዬ ነው፤ በእ​ር​ሱም እታ​መ​ና​ለሁ፤ ጋሻ​ዬና የመ​ድ​ኀ​ኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መድ​ኀ​ኒቴ ሆይ፥ ከግ​ፈኛ ታድ​ነ​ኛ​ለህ።


“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።


በአ​ንተ የሚ​ታ​መ​ኑት ሁሉ ግን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በእ​ነ​ር​ሱም ታድ​ራ​ለህ። ስም​ህ​ንም የሚ​ወ​ድዱ ሁሉ በአ​ንተ ይመ​ካሉ።


በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤


ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤ ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።


የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።


ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው።


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


እና​ንተ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ በፍ​ጹም ልባ​ች​ሁም ከሻ​ች​ሁኝ ታገ​ኙ​ኛ​ላ​ችሁ።


እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፣ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች