Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 49:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አፍህ ክፋ​ትን አበ​ዛች፥ አን​ደ​በ​ት​ህም ሽን​ገ​ላን ተበ​ተ​ባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ብርሃን ከቶ ወደማያዩት፣ ወደ አባቶች ማኅበር ይቀላቀላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም በማድረጉ ይወደሳልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በሞት ተለይቶ ዳግመኛ ብርሃንን ወደማያይበት ወደ ቀድሞ አባቶቹ ይሄዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 49:19
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ግን ወደ አባ​ቶ​ችህ በሰ​ላም ትሄ​ዳ​ለህ፤ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ል​ናም ትቀ​በ​ራ​ለህ።


ባኦ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቴ​ር​ሳም ተቀ​በረ፤ ልጁም ኤላ በአሳ በሃያ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ሕይ​ወ​ቴም በብ​ር​ሃን ውስጥ ታመ​ሰ​ግን ዘንድ፥ እርሱ ነፍ​ሴን ከሞት አድ​ኖ​አ​ታል።


አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።


የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እን​ደ​ም​ት​ወጣ፥ የእ​ን​ስ​ሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እን​ደ​ም​ት​ወ​ርድ የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው።


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች