Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 118:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ምስ​ክ​ር​ህም ትም​ህ​ርቴ ነው፥ ሥር​ዐ​ት​ህም መካሬ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ በርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጌታ የሠራት ቀን ይህች ናት፥ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርሷም ደስ ይበለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ይህ እግዚአብሔር የሠራው የድል ቀን ነው፤ በእርሱ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 118:24
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ እነ​ር​ሱም ንጉ​ሡን መረቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለባ​ሪ​ያው ለዳ​ዊ​ትና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት ሁሉ በል​ባ​ቸው ደስ ብሏ​ቸው፥ ሐሴ​ትም አድ​ር​ገው ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።


እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


በኢያሱ ፊት ያኖርሁት ድንጋይ እነሆ አለ፣ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፣ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።


ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመ​ባ​ረክ ተሰ​ብ​ስ​በን ሳለን ጳው​ሎስ በማ​ግ​ሥቱ የሚ​ሄድ ነውና ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመረ፤ እስከ መን​ፈቀ ሌሊ​ትም ድረስ ትም​ህ​ር​ቱን አስ​ረ​ዘመ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች