Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 19:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፥ ከዐስበ ደነስ ጋር የሚቀርብ ስእለትም ንጹሕ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሰነፍ ልጅ ለአባቱ ኀዘን ነው፥ ጠበኛም ሚስት ሳያቋርጥ እንደሚያንጠባጥብ ውሃ ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሞኝ ልጅ አባቱን ወደ ጥፋት ያደርሳል፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 19:13
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ውኆች ድን​ጋ​ዮ​ችን ይፍ​ቃሉ፤ ፈሳ​ሾ​ቹም የም​ድ​ሩን አፈር ይወ​ስ​ዳሉ፤ እን​ዲሁ አንተ የሰ​ውን ተስፋ ታጠ​ፋ​ዋ​ለህ።


ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል።


ብልህ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ አላዋቂ ልጅ ግን እናቱን ያሰድባል።


ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ ወንድሞች በመከራ ጊዜ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፥ ስለዚህ ይወለዳሉና።


የሰነፍ ልብ ገንዘብ ላደረጋት ኀዘን ናት፥ አባት ባልተማረ ልጁ ደስ አይለውም፥ ብልህ ልጅ ግን እናቱን ደስ ያሰኛል።


አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ኀዘን ነው።


ከቍጡ፥ ከነዝናዛና ከነገረኛ ሴት ጋር ከመቀመጥ ይልቅ በምድረ በዳ መቀመጥ ይሻላል።


ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች