Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እጅ መንሻ ለሰጪው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤ በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቁ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንዳንድ ሰዎች ጉቦ እንደ አስማት የሚሠራ ይመስላቸዋል፤ ጉቦ በመስጠትም ሁሉ ነገር ይሳካልናል ብለው ያምናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 17:8
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁለት መቶ እን​ስት ፍየ​ሎ​ች​ንና ሃያ የፍ​የል አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሁለት መቶ እን​ስት በጎ​ች​ንና ሃያ የበግ አው​ራ​ዎ​ችን፥


እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።


አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እን​ዳ​ዳ​ነው ዛሬ ዐወ​ቅሁ፤ ከሰ​ማይ መቅ​ደሱ ይመ​ል​ስ​ለ​ታል በቀኙ የማ​ዳን ኀይል።


ለመ​ን​ጠቅ እን​ደ​ሚ​ያ​ሸ​ምቅ አን​በሳ በላዬ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ።


ጻድ​ቃን ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለቅ​ድ​ስ​ና​ውም መታ​ሰ​ቢያ አመ​ስ​ግኑ።


መማ​ለ​ጃን አት​ቀ​በል፤ መማ​ለጃ የዐ​ይ​ና​ማ​ዎ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ እው​ነ​ተኛ ቃል​ንም ያጣ​ም​ማ​ልና።


መማለጃን በዐመፃ በብብቱ የሚቀበል መንገዶቹን አያቀናም፥ ክፉ ሰውም ከጽድቅ መንገዶች ይርቃል።


ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።


በስውር ያለ ስጦታ ቍጣን ይመልሳል፥ ስጦታን የሚሸልግ ግን ጽኑ ቍጣን ያስነሣል።


ግፍ ጠቢ​ብን ያሳ​ብ​ደ​ዋል፥ የል​ቡ​ንም ትዕ​ግ​ሥት ያጠ​ፋ​ዋል።


አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


ጻድ​ቁን የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጉቦ​ንም የም​ት​ቀ​በሉ፥ በበ​ሩም የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ፍርድ የም​ታ​ጣ​ምሙ እና​ንተ ሆይ! በደ​ላ​ችሁ እን​ዴት እንደ በዛ፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም እን​ዴት እንደ ጸና እኔ ዐው​ቃ​ለ​ሁና።


እጆቻቸውን ለክፋት ያነሣሉ፥ አለቃውና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፥ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጕናሉ።


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


ዳዊ​ትም ያመ​ጣ​ች​ውን ከእ​ጅዋ ተቀ​ብሎ፥ “በሰ​ላም ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እነሆ፥ ቃል​ሽን እንደ ሰማሁ፥ ፊት​ሽ​ንም እን​ዳ​ከ​በ​ርሁ ተመ​ል​ከቺ” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች