ዘኍል 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ፥ ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እንደዚሁም ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አቅርቡ፤ ይህም ለሚቃጠል መሥዋዕት ሲሆን ሽታው ደስ የሚያሰኝና በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋር በዘይት የተለወሰ የእህል ቊርባን አንድ ኪሎ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ መባ ሆኖ ይቀርባል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |