Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ዚህ ሰዎች ሰው እን​ደ​ሚ​ሞት ቢሞቱ፥ ወይም መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ሰው ሁሉ መቅ​ሠ​ፍት ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነዚህ ሰዎች እንደ ማንኛውም ሰው አሟሟት የሚሞቱ ቢሆኑና በሌሎች ሰዎች ላይ የሚደርሰው ብቻ የሚደርስባቸው ከሆነ፣ እኔን እግዚአብሔር አልላከኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነዚህ ሰዎች በተፈጥሮ ሰው እንደሚሞተው ቢሞቱ፥ ወይም ሰው ሁሉ እንደሚቀበለው የዕጣ ክፍሉ የሚቀበሉ ቢሆን እኔን ጌታ አልላከኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነዚህ ሰዎች ከእግዚአብሔር ቅጣት ሳይደርስባቸው እንደማንኛውም ሰው ከሞቱ፥ እኔን እግዚአብሔር አላከኝም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነዚህ ሰዎች ሰው እንደሚሞት ቢሞቱ፥ ወይም እንደ ሰው ሁሉ ቢቀሠፉ እግዚአብሔር አልላከኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:29
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነቢዩ ኤል​ያ​ስም ወደ ሰማይ አቅ​ንቶ ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእ​ሳት ስማኝ፤ አንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪ​ያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህ​ንም ሥራ ስለ አንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች ይወቁ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።


ሚክ​ያ​ስም፥ “በደ​ኅና ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ አል​ተ​ና​ገ​ረም” አለ። “ደግ​ሞም እና​ንተ ሕዝቡ ሁሉ ስሙኝ” አለ።


አሁን ቍጣ​ውን የሚ​ያ​ውቅ የለ​ምና፥ ታላቅ ኀጢ​አ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለ​ምና።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


አሁ​ንም ሂድ፤ ይህ​ንም ሕዝብ ወደ ነገ​ር​ሁህ ቦታ ምራ፤ እነሆ፥ መል​አኬ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል፤ ነገር ግን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ቀን ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


ለሰው ልጆች ሞት አለ​ባ​ቸው፥ ለእ​ን​ስ​ሳም ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንድ ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንዱ እን​ደ​ሚ​ሞት ሌላ​ውም እን​ዲሁ ይሞ​ታል፤ ለሁ​ሉም አንድ እስ​ት​ን​ፋስ አላ​ቸው፥ ሰው ከእ​ን​ስሳ ብል​ጫው ምን​ድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለ​ውም።


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


በውኑ ስለ እነ​ዚህ ነገ​ሮች አል​ቀ​ሥ​ፍ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?


ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።


ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች