Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈ​ጥር፥ ምድ​ርም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤታ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ና​ቸ​ውን፥ ለእ​ነ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ብት​ው​ጣ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ፥ ያን​ጊዜ እነ​ዚህ ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አስ​ቈጡ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ፈጽሞ አዲስ የሆነ ነገር አምጥቶ ምድር አፏን ከፍታ እነርሱንና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ብትውጥና በሕይወታቸው ወደ መቃብር ቢወርዱ፣ ሰዎቹ እግዚአብሔርን የናቁ መሆናቸውን የምታውቁት ያን ጊዜ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ጌታ ግን አንድ አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያንጊዜ እነዚህ ሰዎች ጌታን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ነገር ግን እግዚአብሔር ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ነገር በመፍጠር በሕይወታቸው ሳሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዱ ዘንድ ምድር ተከፍታ እነርሱንና የእነርሱ የሆነውን ሁሉ ብትውጥ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የተቃወሙ መሆናቸውን ታውቃላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈጥር፥ ምድርም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ለእነርሱም ያለውን ሁሉ ብትውጣቸው፥ በሕይወታቸውም ወደ ሲኦል ቢወርዱ፥ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ ናቁ ታውቃላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:30
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋንታ ከላይ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ ርስት ከአ​ር​ያም ምን​ድን ነው?


ሞት ለዐ​መ​ፀኛ፥ መለ​የ​ትም ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠሩ ነው።


ጻድ​ቃን እጃ​ቸ​ውን በዐ​መፃ እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኃ​ጥ​ኣ​ንን በትር በጻ​ድ​ቃን ዕጣ ላይ አይ​ተ​ው​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በኃ​ጥ​ኣን ተራራ እንደ ነበረ ይነ​ሣል፤ በገ​ባ​ዖን ሸለ​ቆም ይኖ​ራል፤ ሥራ​ውን ማለት መራራ ሥራ​ውን በቍጣ ይሠ​ራል፤ ቍጣ​ውም ድን​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ መር​ዙም ልዩ ነው።


እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እኔ ምድ​ርን ሠር​ቻ​ለሁ፤ ሰው​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ቼ​አ​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አዝ​ዣ​ለሁ።


ብር​ሃ​ንን ፈጠ​ርሁ፤ ጨለ​ማ​ው​ንም ፈጠ​ርሁ፤ ሰላ​ም​ንም አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፋ​ት​ንም አመ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ያደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።


አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዣ​ለሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥ​ሮ​አ​ልና ሰው ወደ ድኅ​ነት ይመ​ጣል።”


በው​ኃው አጠ​ገብ ያሉ የዕ​ን​ጨ​ቶች ሁሉ ቁመት እን​ዳ​ይ​ረ​ዝም ራሱም ወደ ደመና እን​ዳ​ይ​ደ​ርስ ያንም ውኃ የሚ​ጠ​ጡት እን​ጨ​ቶች ሁሉ በር​ዝ​መ​ታ​ቸው ከእ​ርሱ ጋራ እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከሉ ሁሉም ወደ መቃ​ብር በሚ​ወ​ርዱ ሰዎች መካ​ከል በጥ​ልቅ ምድር ሞቱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መና​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ ከበ​ታ​ቻ​ቸው ያለ​ችው መሬት ተሰ​ነ​ጠ​ቀች፤


እነ​ር​ሱም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በሩ ሁሉ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድ​ሪ​ቱም ተዘ​ጋ​ች​ባ​ቸው፤ ከማ​ኅ​በ​ሩም መካ​ከል ጠፉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች