Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 14:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 በነ​ጋ​ውም ማል​ደው ተነሡ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ራስ ወጥ​ተው፥ “እነሆ፥ እኛ ከዚህ አለን፤ በድ​ለ​ና​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ስፍራ እን​ወ​ጣ​ለን” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 በማግስቱም ጧት ማልደው ወደ ተራራማው አገር ወጡ፤ እንዲህም አሉ፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጠን ስፍራ እንወጣለን”።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በማግስቱም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ እንዲህ እያሉ ወጡ፦ እነሆ፥ እኛ በዚህ አለን፤ እኛ ኃጢአትን ሠርተናልና ጌታ ወዳለው ስፍራ እንወጣለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በማግስቱ ጠዋት ማልደው ተራራማይቱን አገር ለመውረር ተነሡ፤ እንዲህም አሉ፦ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊያስገባን ወደነገረን ስፍራ ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ ኃጢአት መሥራታችንን ተገንዝበናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 በነጋውም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ ወጥተው፦ እነሆ፥ መጣን፤ እኛ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 14:40
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


የሀ​ገር ልጅ ቢሆ​ንም ወይም መጻ​ተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕ​ቢ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰድ​ቦ​አል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል።


በለ​ዓ​ምም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አንተ በመ​ን​ገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆም​ህ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ እን​ግ​ዲህ አሁን አት​ወ​ድድ እን​ደ​ሆነ እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።


ባለ​ቤቱ ተነ​ሥቶ ደጁን ይዘ​ጋ​ልና፤ ያን​ጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈ​ት​ልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀ​ም​ራሉ፤ መል​ሶም፦ ከወ​ዴት እንደ ሆና​ችሁ አላ​ው​ቃ​ች​ሁም ይላ​ቸ​ዋል።


“እና​ን​ተም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ናል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ሁሉ እን​ወ​ጣ​ለን፤ እን​ዋ​ጋ​ማ​ለን ብላ​ችሁ መለ​ሳ​ች​ሁ​ልኝ። ከእ​ና​ን​ተም ሰው ሁሉ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ያዘ፤ ወደ ተራ​ራም ወጣ​ችሁ።


እኔም ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ እና​ንተ ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ተላ​ለ​ፋ​ችሁ፤ በኀ​ይ​ላ​ች​ሁም ወደ ተራ​ራ​ማው አገር ወጣ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች